የፋይናንስ አቅም ፕሮግራም
የክሬዲት፣ የዕዳ ጉዳዮችን ይፍቱ እና የፋይናንስ
ክህሎቶችን ይገንቡ!
Financial Capability (የፋይናንስ አቅም) ፕሮግራም ነዋሪዎቻችን የፋይናንስ እውቀታቸውን እንዲያጠናክሩ፣ ሊተገበሩ የሚችሉ የገንዘብ አያያዝ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እና ዘላቂ መረጋጋት ለማግኘት የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ለመርዳት የተዘጋጀ ነው።76
-

የፋይናንስ ሥልጠና
ተሳታፊዎች በፋይናንስ ባለሙያዎች የሚሰጥ 1 ለ1 ሥልጠና ያገኛሉ። በ4 ክፍለ ጊዜዎች የቤተሰብ በጀት ያዘጋጃሉ፣ ችግሮችን ለመፍታት የክሬዲት ሪፖርቶችን ይገመግማሉ እንዲሁም የቁጠባ የባንክ ሒሳቦችን ይከፍታሉ።
-

የቡድን ወርክሾፖች
እነዚህ ክፍለ ጊዜዎች የባንክ አገልግሎቶች እና የቁጠባ ክህሎቶችን ይሸፍናሉ። የማጭበርበር ሥራዎችን እና ደኅንነታችው የተጠበቁ የባንክ አጠቃቀም ልምዶችን ይለዩ፣ ዕዳዎን ያስተዳድሩ፣ ክሬዲት ምን ማለት እንደሆነ እና የክሬዲት ነጥብዎን እንዴት ማሻሻል እንደሚችሉ ይገንዘቡ እንዲሁም የሸማች መብቶችን እና ውጤታማ በሆነ መልኩ መብትዎን ማስጠበቅ የሚችሉባቸውን ስልቶች ይወቁ።
-

ተዛማጅ የቁጠባ ድጎማ ፕሮግራም
የHRI Matched Savings ፕሮግራም። ከ6-8 ወራት ውስጥ እንዲደረስበት ከታቀደ የ$1,000 የቁጠባ ግብ ጋር። HRI ተሳታፊዎች ከሚቆጥቡትን መጠን ጋር 2:1 በሆነ ውድር ተዛማጅ የሆነ የቁጠባ ድጎማ ይሰጣል። በድምሩ የቁጠባ ገንዘብ $2000 ይሆናል!
የፕሮግራም ዝርዝሮች
የስፕሪንግ (ፀደይ) ቡድን፦ እ.ኤ.አ ከጃኑዋሪ ወር - ሜይ ወር 2026 ዓ.ም
የማመልከቻ ቀነ ገደብ፦ እ.ኤ.አ አርብ፣ ዲሴምበር 12 ቀን 2025 ዓ.ም
ያለው ቦታ በ40 ግለሰቦች የተገደበ ነው። እ.ኤ.አ በኤፕሪል እና ሜይ ወር የሚካሄዱ ወርክሾፖች
የብቁነት መስፈርቶች፦
በዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ የHRI ነዋሪዎች በሙሉ እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ። ምንም የገቢ ደረጃ ገደቦች የሉም። ማመልከቻውን በመሙላት ዙሪያ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት እባክዎ የሚከተሉትን ያነጋግሩ፦
Joe Deignanን በjdeignan@homeownersrehab.org
የፋይናንስ ሥልጠና
የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በ8-ሳምንታት ውስጥ በፋይናንስ አሠልጣኝ አንድ ለአንድ የሚሰጡ እና ለ1 ሰዓት የሚዘልቁ አራት ክፍለ ጊዜዎች ላይ ይታደማሉ። ከCambridge Economic Opportunity Commission (የCambridge የኢኮኖሚያዊ ዕድሎች ኮሚሽን፣ CEOC) ጋር በመተባበር የሥልጠና ክፍለ ጊዜዎቹ የሚከተሉትን ነገሮች በመፍታት ረገድ ለተሳታፊዎች ድጋፍ ይሰጣሉ፦
የቤተሰብ በጀት ለማዘጋጀት
የክሬዲት ሪፖርት ለመገምገም እና የክሬዲት ነጥብን ለመለየት
ከሚከተሉት ውስጥ ለአንዱ ወይም ከዚያ በላይ ለሚሆኑት፦
የቁጠባ/ተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት
ዕዳ(ዎች)ን መልሶ ለመክፈል እና/ወይም በመጠባበቅ ላይ ያለ የክሬዲት ችግር ለመፍታት ዕቅድ ለማውጣት
በፕሮግራም የተፈቀደ ሌላ ግብ(ቦች)
የቡድን ወርክሾፖች
8 ሳምንት በሚዘልቀው ፕሮግራም ወቅት ተሳታፊዎች 4 ሰዓታት የሚሸፍኑ የቡድን የfinancial capability ወርክሾፖችንም መታደም ይጠበቅባቸዋል። እነዚህ ክፍለ ጊዜዎች የሚከተሉትን ይሸፍናሉ፦
የባንክ አገልግሎት እና የቁጠባ መሣሪያዎች
ማጭበርበር እና ደኅንነቱ የተጠበቀ የባንክ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ምርጥ አሠራሮች።
የዕዳ አስተዳደር እና ምርጥ አሠራሮች።
ክሬዲትን እና የክሬዲት ነጥብን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል መረዳት።
የሸማች መብቶች እና ውጤታማ የሆኑ የራስን መብት ማስጠበቂያ ስልቶች።
ሥልጠናው እና የቡድን ክፍለ ጊዜዎቹን በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ በኋላ ፍላጎት ያላቸው ተሳታፊዎች ይመረቁ እና Matched Savings ፕሮግራም በተሰኘው ቀጣዩ የፕሮግራም ምዕራፍ ለመሳተፍ ማመልከት ይችላሉ።
ተዛማጅ የቁጠባ ድጎማ ፕሮግራም
መላውን የፋይናንስ ሥልጠና እና የቡድን ወርክሾፖች በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ በኋላ ተሳታፊዎች ለHRI match savings ፕሮግራም ብቁ ይሆናሉ!
The Midas Collaborative ጋር በመተባበር ብቁ የሆኑ የፕሮግራም ተሳታፊዎች ከ6-8 ወራት ውስጥ የሚደረስበት $1,000 የመቆጠብ ግብ በማስቀመጥ ለዚህ ዓላማ የሚውል የቁጠባ ሒሳብ ይከፍታሉ። ግቡ ላይ ከተደረሰ በኋላ HRI 2:1 በሆነ ተመን በጠቅላላው በ$2,000 ከተሳታፊው ቁጠባዎች ጋር የሚዛመድ የቁጠባ ገንዘብ ድጎማ ያደርጋል። ተሳታፊዎች ተዛማጅ የቁጠባ ገንዘብ ድጎማዎችን ማግኘት የሚችሉት የ$1,000 ቁጠባ ግቡን ካጠናቀቁ በኋላ ብቻ ነው።
ተሳታፊዎች በዚህ ተዛማጅ የቁጠባ ድጎማ የሚደረግበት የቁጠባ ሒሳብ ውስጥ የሚገኙትን ገንዘቦች በመጠቀም ብቁ ንብረቶችን መግዛት ይችላሉ። ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦ የመኪና ግዢ፣ የኮሌጅ ወይም ትምህርታዊ ወጪዎች፣ ትላልቅ የቤት እቃዎች፣ የዕዳ ወይም የክሬዲት ችግር መፍታት ወይም ሌሎች ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ ግዢዎች።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ያነጋግሩ፦
Joe Deignan (እሱ/የእሱ)
Director of Community Engagement (የማኅበረሰብ ተሳትፎ ዳይሬክተር)
ስልክ፦ 617.868.4858 መስመር 210 | ሞባይል፦ 617-682-9666
ኢሜይል፦ jdeignan@homeownersrehab.org

